Skip to content

የካምብሪጅ መኖሪያ አባልነት

ሙዚየሙ ለካምብሪጅ መኖሪያ አባላት አጠቃላይ መግቢያ ከክፍያ ነጻ ሲያቀርብ ደስታ ይሰማዋል!

የካምብሪጅ ነዋሪ ነዎት? ነጻ የካምብሪጅ መኖሪያ አባልነትን ከክፍያ ነጻ ለማግኘት ይመዝገቡ እና እርሶ እና ቤተሰብዎ ሙዚየም በሚጎበኙበት ጊዜ የሚሰጥ የነጻ መግቢያ ተጠቃሚ ይሁኑ። እባክዎ ያስታውሱ፡ የምዝገባ ገጹ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ብቻ የተዘጋጀ ነው። የትርጉም አገልግሎቶች በ ሙዚየሙ የእንግዳ መቀበያ ዴስክ ላይ ሊገኙ ይችላሉ፣ በዚያም የጎብኚዎች ቆይታ ቡድን አባላት እርሶን ለመርዳት ደስተኞች ናችው።

ይህ የካምብሪጅ የመኖሪያ አባልነት ካርድ ከ አንድ ቤተሰብ ሁለት አዋቂዎችን እና በተመሳሳይ አድራሻ ላይ የሚኖሩ ከ 18 አመት በታች የሆኑ ልጆችን ይቀበላል። ከእያንዳንዱ ቤት ውስጥ ከሁለት በላይ የሆኑ አዋቂ ሰዎች መመዝገብ ይችላሉ። ከዚህም በተጨማሪ የካምብሪጅ መኖሪያ አባላት በየወሩ ቀጣይ የሚዘጋጁ መርሃ-ግብሮች መረጃ፣ የኤግዚቢሽን ዋና ዋና መገለጫዎች እና ሌሎችም አስደሳች የሆኑ ይዘቶችን የያዘ የዜና መጽሔት ይደርሳቸዋል።