Skip to content

AI: በመሃል ያለውን ልዩነት አስተውል (AI: Mind the Gap)

የሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ (artificial intelligence (AI)) የሚገርመው ነገር፣ የሰው ልጅ በሚኖሩት ተሞክሮ ላይ እና የሰው ልጅ አሰተሳሰብ ተፈጥሮ ላይ አዳዲስ እይታዎች እንዲኖሩ የሚያበረታታ መሆኑ ነው። ከዚያም እነዚህ እይታዎች የሰውን ልጅ የመሰለ አስተሳሰብ በማሽኖች ላይ እንዲኖር በማድረግ ላይ ተግባር ላይ ይውላሉ። Claude Shannon፣ Seymour Papert እና የሌሎችም በሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ፣ ትምህርታዊ ቴክኖሎጂ፣ የመረጃ ንድፈ-ሃስብ ላይ ጀማሪ ስራቸውን ከሰሩ በኋላ የ MIT ተመራማሪዎች አሁን ድረስ እያደገ የሚገኘውን የሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ ላይ የተመረኮዘ መጪ ጊዜ በመፍጠር ላይ ግንባር ቀደም ተዋንያን ሆነው ቆይተዋል። አሁን በዚህ ኤግዚብሽን ላይ የቀረበው ምርምር በኮምፒውተር ሳይንስ፣ ሜካኒካል ምህንድስና፣ ኔይሮሳይንስ እና ማሕበራዊ ሳይንስ የትምህርት ዘርፎች ላይ አስቀድመው በተሰሩ ስራዎች ትከሻ ላይ የቆመ ነው። ይህ ምርምር በሰው ልጅ እና በማሽን የማሰብ ችሎታ መሃከል ያለውን ግንኙነት በገለጸ ቁጥር፣ በነዚህ ሁለቱ መሀል ያለውን ልዩነት የበለጠ ግልጽ እያደረገው ይመጣል። የዚህ ቴክኖሎጂ፣ ከቤት ውስጥ ከሚገኘው AI ጀምሮ እስከ በስራ ቦታ ላይ የሚገኙት ሮቦቶች ድረስ በብዙ ቦታ ላይ መገኘት፣ ይህ ቴክኖሎጂ ያለው አቅም፣ የሚያስከትላቸው አደጋዎች እና የማሽን ችሎታ ከሰው ልጅ ችሎታ ጋር ያለው ንጽጽር አስመልክተን ጥያቄዎችን እንድንጠይቅ ያስገድደናል። ግልጽ እየሆነ የመጣው ነገር፣ ሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታን እና የማሽን የመማር ችሎታን ባሳደግነው ቁጥር፣ በመሃላቸው ያለውን ልዩነት ግምት እያስገባን መሄድ ይኖርብናል።