Skip to content

የወደፊቱ ዓይነት (Future Type)

ብዙውን ጊዜ የኮምፒውተር ኮድ ለቴክኒካዊ አገልግሎት ብቻ ጥቅም ላይ የሚውል ውስብስብ እና ድርቅ ያለ ነገር እንደሆነ እናስባለን። ነገር ግን ኮድ በሠዓሊዎችና በንድፍ አውጪዎች እንደፈጠራ መሣሪያ ጥቅም ላይ ሊውል የሚችለው እንዴት ነው? ይህ ጥያቄ በMIT Media Lab የሚሰራውን Future Sketches ቡድን ይበልጥ እንዲነሳሳ ያደርገዋል። በአርቲስት እና በመምህር Zach Lieberman የሚመራው ይህ ቡድን ጥበባዊ ቁጥጥር የተደረገባቸው፣ በኮምዩተር የተፈጠሩ እይታዎች እንዲሆን አድርጎ በመጠቀም ኮድን “ማየት” እንድንችል የማገዝ ዓላማ አለው።

በዚህ ኤግዚቢሽን ውስጥ የሚገኙት የእይታ አይነቶች ከቲፖግራፊ ተወስደው የተሳሉ እና የተለያዩ የፕሮግራም ቋንቋዎችን በመጠቀም በዲጂታል ስርዓት የተፈጠሩ ናቸው። አንድን ቃል ማንቀሳቀስ የአንድን ዓረፍተ ነገር ትርጉም ሊለውጥ እንደሚችለው ሁሉ ኮድ ላይ የሚደረጉ ጥቃቅን ለውጦችም በጣም የተለያየ ውጤት ሊያስከትሉ ይችላሉ። የፈጠራ ኮድ ከእነዚህ አነስተኛ ማስተካከያዎች የሚመጡ ያልተጠበቁ እና አስገራሚ ውጤቶችን በደስታ ይቀበላል። በዚህ ስነ-ጥበብ ውስጥ ቋንቋው ቀለምም ሸራም ነው።

ምንም እንኳን በአንዳንድ ዘመናዊ የዲጂታል መሣሪያዎች የተሠራ ቢሆንም፣ የFuture Sketches ስራ የሥነ ጥበብ ሥራዎችን ለመስራት የረጅም ጊዜ ስርዓታዊ አቀራረቦች ዘዴ ወይም አቀራረቦች ውስጥ ስር የሰደደ ነው። ትናንሽ ልውጠቶች እና ሽግግሮች አንድ ሰዓሊ በማናቸውም መልኩ ሊያስባቸው የማይችላቸውን ጥበባዊ ቅጦችን የሚፈጥሩ ሲሆን ውጤቶቹ ደግሞ የድንቃይ ስና ድማሜ ስሜቶችን ሊያነቃ ይችላል። Future Sketches ከዚህ ቀደም የነበሩ መሳሪያዎችን በመጠቀም እና ለቀጣይ ትውልድ የስነ-ጥበብ ስሌታዊ አገላለጽ አገላለጽ አዳዲስ መሳሪያዎችን በመፍጠር፣ በመገንባት እና በመደገፍ ይህን ማሳካት ይችላሉ።

ዛክ ሊበርማን
የሰውነት ንድፍ (ዓይነት)፣ 2024
ዲጂታል ተሳታፊ

የሰው ልጅ ድርጊት በኮድ እውቅና ሊያገኝ እና ሊሸጋገር የሚችለው እንዴት ነው? Lieberman በንድፍ ሥራው ሂደት ውስጥ እንዲህ ያሉ የተለያዩ ክፍት ጥያቄዎችን ይመረምራል። ልክ እንደ እርሳስ ንድፍ፣ የLieberman የኮድ ንድፎች በአንጻራዊ ሁኔታ በፍጥነት የተሠሩ ሲሆን እነዚህም ለሱ ይበልጥ ሊያጎለብተው የሚችለውን የመጀመርያውን ሃሳብ የሚመረምርበት መንገድ ነው። ብዙውን ጊዜ በእይታዊ አገላለጽ ስሌት እና ቲፖግራፊ እንደሚፈተሸበት አንድ መንገድ ንድፎችን ከእንቅስቃሴ እና ከሰው ልጅ አካል ጋር ያስተሳስረዋል።

ቬራ ቫን ደ ሲፕ
የተጠለፈ ዓይነት፣ 2023
የእንጨት ፍሬም ላይ ማሽን-የተንጠለጠሉ ክር

ይህ ሥራ የተጀመረው የፊደል ቅርጾችን እንቅስቃሴ እንደሚቃኝ አንድ ዲጂታል አኒሜሽን ሆኖ ነበር። ከዚያም ቫን ደ ሲፕ አንድን አኒሜሽን ወደተከታታይ የቆሙ ምስሎች የሚቀይር በበይነ መረብ ማሰሻ ላይ የተመሰረተ አንድ መሳሪያ ፈጠረች። የፒክሰሎችን መስመር ከቆሙ ምስሎች ወደ ኒቲንግ ፓተርን መስመር መቀየር የሚችል ሌላ መሰርያ ፈጠረች። በ1980ዎቹ የተሻሻለ ፕሮግራም መደረግ የሚችል ኒቲንግ ማሽን በመጠቀም፣ እዚህ የሚታዩትን አይነት ኒትድ ማትሪክስ ፈጠረች። ስራውን ወደ መጀመርያው ቅርጹ የመመለስ እና ትርጉምና አስታራቂነት በዲዛይን ላይ እንዴት ተጽእኖ ሊያሳድር እንደሚችል በመፈተሸ፣ ቫን ደ ሲፕ የጥልፍ ስራውን ፎቶግራፍ አንስታ ልክ እንደ አኒሜሽን በአንድ ፍሊፕቡክ ውስጥ መልሳ አንድ ላይ ለጠፈችው።

ሊንግዶንግ Huang
Bendy ዓይነት, 2024
3D-የታተመ ፕላስቲክ ፋይላሜንት

ሁዋንግ ከማንኛውም ቅርጽ ወደ ማንኛውም ቅርጽ መለወጥ የሚችል ለማወቅ የሚያጓጓ አንድ አልጎሪዝም አጎልብቷል። ቲፖግራፊ ላይ ተግባራዊ ሲደረግ፣ ይህ ለውጥ አንዱ ፊደል ከሌላው ፊደል ጋር ቀና እና እንከን የለሽ ግንኙነት እንዲኖር አድርጓል። ይህ አኒሜሽን ስክሪን ላይ እነዚህን ቀስ በቀስ የሚከሰቱትን ሽግግሮች ምሳሌዎች ያሳያል። የሙከራዎቹ 3D ሀትመቶች የፊደሎችን እጥፋት በተጨባጭ ቅርጽ የሚያሳዩ ቲፖግራፊክ ቅርጾችን ፈጥረዋል።

ቻር ስታይልስ
ኦሎምፒክ ፎርምስ፣ 2024
ዲጂታል ተሳታፊ

ይህ የአጻጻፍ አይነት የተዘጋጀው በኦፕንፍሬምዎርክስ ኤንድ ኦፕንሲቪ በተሠራ አንድ መተግበርያ አማከይነት የኦሎምፒክ አትሌቶችን ፉቴጅ በማቀናበር ነው። ይህ መተግበርያ የአካል ክፍሎች መከፋፈያ አልጎሪዝም በመጠቀም ከፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ የቪዲዮ ስርጭት የአትሌቶችን አካላዊ ሁኔታዎች ለይቷል። ከዚያም እያንዳንዱ አካላዊ ሁኔታ ይፋ በተደረገው የፓሪስ ኦሎምፒክ ፎንት ውስጥ ካሉ ፊደሎች ቅርጾች፣ እንደ ጂምናስቲክ ካሉ ስፖርቶች፣ ከስኬትቦርዲንግ እና ምርጥ ግጥሚያዎችን ካሳዩ ሌሎች ስፖርቶች ቅርጽ ጋር ተነጻጽሯል።

ዛክ ሊበርማን
ዓይነት ዓለም, 2016–2024
ባለ ሶስት ቻናል ቪድዮ በ ድምፃዊ Daito Manabe, 8 00

ንድፍ አውጪዎች ታይፕን የሚቀይሩት እና የሚያሸጋግሩት እንዴት ነው? በዚህ መሳጭ አኒሜሽን ውስጥ፣ Lieberman ቅርጾች ፊደል፣ ፊደሎች ቃላት እና ቃላት ዓረፍተ ነገሮች የሚሆኑበትን አስደናቂ ዓለም ፈጥሯል። አንድ አይነተኛ ታሪክ ከሚቀርብበት አንድ ተራኪ ቪድዮ ይልቅ፣ Lieberman የሱን አኒሜሽኖች “ተንቀሳቃሽ ስዕሎች” ሲል ይገልጻቸዋል - ግራፊካዊ ቅርጽን፣ አዲስ ዲዛይን፣ ስሌትን እና ቲፖግራፊያዊ አገላለጽን የሚፈትሹ እይታዊ አካባቢዎች ናቸው።

ከFuture Sketches ግሩፕ በቲፖግራፊ ላይ የተደረጉ ሙከራዎች

1. Vera van de Seyp, Assorted Type Tools, 2023–2024

2. Lingdong Huang, Alternative Type Exploration, 2024

3. Vera van de Seyp, 36 Days of Type, 2023

4. Vera van de Seyp, Tomorrow’s Typography, 2023–2024

5. Lingdong Huang, Photographic Inverse Kinematics, 2024

6. Lingdong Huang and Vera van de Seyp, Body Type, 2022

7. Char Stiles, FKA ASCII, 2023

8. Zach Lieberman, AR Type Experiments, 2022