Skip to content

Ganson

እነዚህ ማሽኖች የኮምፒውተር ፕሮግራሞች፣ ባለሦስት አውታር ምህዳር ላይ እንዲገለጡ በማድረግ ግዑዝ አካል እንዲለብሱ የተደረጉ የቁም ቅዠቶች እንደማለት ናቸው። - Arthur Ganson

በኪን እና በሳይንስ መካከል ያለውን መስመር እንዲደበዝዝ የሚያደርግን ሥራ ያመረተው Arthur Ganson ራሱን ሲያስተዋውቅ ሜካኒካል ኢንጂነር መሃንዲስ በመሆን እና የጭፈራ አቀናባሪ በመሆን መካከል የተዳቀለ እንደሆነ አድርጎ ይጠቅሳል። የእርሱ መግባቢያ በግዑዝ ዓለም ውስጥ እምብዛም በማይስተዋሉ እንቅስቃሴዎች እና ምልክቶች አማካይነት በኮድ የተመሰጠረ ስሜት ወይም አሳብ ነው።

የGanson የአዳዲስ አሳቦች ምንጮች የሚባሉት በአከባቢው ከሚገኙ ከሚያስተውላቸው ነገሮች - በተለምዶ ከማይስተዋሉ የወረቀት ኮሽታዎች ጀምሮ እስከ ህልቁ መሳፍርት መስክ ካሉ ዝርግ ነገሮች ጭምር ይመነጫሉ። በዓይነተኛነት የሚታወቅበት ድብልቅ የሜካኒካዊ ፈጠራ እና ግርምት ፈጣሪ ማንነት ያለው መሆኑ ተዳምሮ፣ የሠራቸውን ሥራዎች ስለ MIT "አዕምሮ እና እጅ" እምነት በዓይነቱ ልዩ ምልከታ ያላቸው ያደርገዋል።

በ1995 በMIT ሬዚደንት ከያኒ ሆኖ በቆየባቸው ጊዜያት፣ "ጥበብ የተላበሱ ማሽኖችን" ዲዛይን ስለማድረግ ለምህንድስና ተማሪዎች አሰልጣኝ ከነበረበት ጊዜ አንስቶ እስካሁኑ ትዕይንት ድረስ፣ Ganson ሌሎችን ስለእያንዳቸው ማሽኖች ምንነት በተመለከተ ምናባቸውን እንዲጠቀሙ እና የራሳቸው ድምዳሜ ላይ እንዲደርሱ እያደረገ ከራሱ ምልከታ በመነሳት ሲገነባ ነበር።

Ganson ራሱ እንደሚናገረው፣ "ስለነዚህ ነገሮች የሚሰሟችሁ ስሜቶች ሁሉ ለእናንተ ዕውነት ናቸው።"