

ቅዠት ውስጥ ያሉ ባህሎች (Hallucinating Traditions)
የAkšamija ምስሎች እንዲሁም በርካታ የባህላዊ አልባስ ዋቢዎች ለላቀ የAI ሶፍትዌር የማሰልጠኛ መረጃ ሆነው ጥቅም ላይ ውለዋል። በዚህ ምክንያት የተከሰቱት በAI የተፈጠሩት የሄድጊር ዲዛይኖች ታሪካዊ ልማዶችን በማጣቀስ ትናንት እና ነገን አደብዝዘው ቴክኖሎጂ ባህላዊ እና ግላዊ የሚሉትን ሁለቱንም አጋላለጾች ለሚቀርበት ለመጪው ጊዜ አንድ መስኮት ከፍተዋል።
በመጨረሻም፣ እነዚህ ግምታዊ ዲዛይኖች ስለ ባህል ያለንን ግንዛቤ የመገዳደር እና ምናብም ሆነ ቴክኖሎጂ ይበልጥ ስር የሰደዱ ባህሎቻችን በመቅረጽ እንዴት ያለ ሚና እንደሚጫወቱ ግንዛቤ ውስጥ እንድናስገባ የመፈታተን እቅድ አላቸው።
ከAI ጋር የተደረገ ውይይት
በትልቁ ስክሪን ላይ እያለፈ ያለው በMerve Akdoğan እና በፕሮጀክቱ ለተፈለገው አላማ እንዲውል በተዘጋጀው የAI ቦት መካከል የተደረገ የተቀረጸ ምልልስ ነው። ባህልን፣ ማንነትን፣ ባህላዊ አግባብነትን፣ ባህላዊ ትውስታን ማቆየትን እና በAI የተያዘውን የተዛባ አመለካከት ጨምሮ በፕሮጀክቱ ላይ የተካተቱን ርዕሰ ጉዳዮች ያንጸባርቃል።
ምስጋና
ቅዠት ውስጥ ያሉ ባህሎች (Hallucinating Traditions)፣ (2024), Azra Akšamija
ሰነዶች፡ የAI አኒሜሽን
አውታሮች (Dimensions)፡ በሆሎግራፊክ ፋን ፕሮጀክተሮች ስክሪን ላይ እንዲወጣ የተደረገ 5-ቻነል ቪድዮ አኒሜሽን
ጥበባዊ ዳይሬክተር፡ Azra Akšamija
የፕሮጀክት ምርምር እና ዝግጅት፡ Merve Akdoğan
ዝግጅት፡ Merve Akdoğan፣ Azra Akšamija፣ Shua Cho