

ራዲካል አቶሞች (Radical Atoms)
ጃፓን ውስጥ ያደገው ሂሮሺ ኢሺ በእናቱ አባከስ ድምፅና ስሜት በጣም ይማረክ ነበር። አባከስ የሂሳብ ስሌት ማሽን ወይም መሳሪያ ነበር፣ ነገር ግን ይህ መሳርያ ለዚያ አንድ ፍሬ ልጅ በጣም ብዙ ነገር ማለት ነበር፡ የሙዚቃ መሳርያ፣ የአሻንጉሊት ባቡር፣ የጀርባ ማከኪያም ነበር። ከዓመታት በኋላ በ1995 ውስጥ, በMIT ሚዲያ ላቦራቶሪ ውስጥ ለአዲሱ የኢሺ Tangible Media Group ከነበሩት መሳጭ እና ቀስቃሽ ነገሮች ውስጥ አንዱ ነበር። በሰው-ከምፒዩተር መስተጋብሮች ላይ ስፔሻሊስት እንደመሆኑ መጠን ኢሺ ሰዎች ከኮምፒዩተሮች ጋር የሚግባቡባቸውን አዳዲስ መንገዶች ለማግኘት ይፈልግ ነበር።
የተጀመረው በ“ታንጅየብል ቢትስ” ራዕይ እና በ“Tangible User Interface” ፈጠራ ነበር። ስክሪን ላይ ያሉ ነገሮችን ለመቀየር ማውሱን ከማንቀሳቀስ ወይም ኪቦርድ ላይ ታይፕ ከማድረግ ይልቅ፣ ተጠቃሚዎች ያለውን መሰረታዊ የኮምፒዩተር ፕሮግራም ለመቆጣጠር (ልክ እንደነዚያ የአባከስ ዶቃዎች) ግዘፍነት ያላቸውን እቃዎች መጠቀም ይችላሉ። እ.ኤ.አ በ2012 ገደማ ኢሺ ይበልጥ አጓጊ የሆነ አንድ ራዕይ አስተዋወቀ፡ “Radical Atoms”። ይህ የዲዛይን ፍልስፍና ማናቸውም እቃ ዲጂታል መረጃን እንዲያሳይ፣ እንዲያካትት እና ምላሽ እንዲሰጥ የሚፈቅዱለትን ተሸጋሪ ቁሶች መፍጠር ላይ ያተኮረ ነበር።
ከ30 ዓመታት በላይ በTangible Media Group እነዚህን ሀሳቦች ለማሳየት በደርዘን የሚቆጠሩ ማራኪ እና ውብ ስራዎችን ሰርቷል። ይህ የሶስት ምስል ስራዎች (SandScape, inFORM) እና ትራንስፎርሜሽን (SandScape) ፣ ኢንፎርሜሽን እና ትራንስፎርሜሽን የሚሉት በሙከራ የተሰሩ ስራዎች ንዑስ ማሽኖቹን ለመሰብሰብ እንዲሁም እንደ ኢሺ አባባል የአተሞች መጨፈር የተጠቃሚ ልምድን ጠብቆ ለማቆየት የMIT ሙዚየም ቀጣይነት ያለው ጥረት አካል ነው።
"ከሕልሜ አንዱ አተሞች እንዲጨፍሩ ማድረግ ነው።"
ሂሮሺ ኢሺ
የራዲካል አተምስ ኤግዚብሽን 2024
እውቅና ማግኘት
ሳንድስኬፕ ፣ 2003
ቤን ፓይፐር፣ ያኦ ዋንግ፣ ካርሎ ራትቲ፣ አሳፍ ቢደርማን፣ ኤራን ቤን-ጆስፔ፣ ሂሮሺ ኢሺ
SandScape፣ MIT ሙዚየም 2022፣ ምርቃት
ኬን ናካጋኪ፣ ኬሩ ዋንግ (NYU)፣ ጆናታን ዊሊያምስ፣ ፓውላ አጊሌራ፣ ሂሮሺ ኢሺ
inFORM፣ 2013-14
ዳንኤል ሊቲንግር፣ ሼን ፎልመር፣ አሌክስ ኦልቫል፣ ፊሊፕ ሾስለር፣ ያሬድ ካውንትስ፣ ኬን ናካጋኪ፣ ዴቪድ ዳን፣ አኪሚትሱ ሆጅ፣ ባሼር ቶሜ፣ ሂሮሺ ኢሺ
Transform፣ 2014
ሂሮሺ ኢሺ፣ ዳንኤል ሌይንገር፣ ሼን ፎልመር፣ አሚት ዞራን፣ ፊሊፕ ሽውስለር፣ ያሬድ ካውንትስ፣ ዳን ሌቪን፣ ሉክ ቪንክ፣ ኬን ናካጋኪ፣ ሺኦ ሺኦ
የMIT ቤተ መዘክር ኤግዚቢሽን ( MIT Museum Exhibition)፣ 2024 (የመልሶ ግንባታ ቡድን)
ፓውላ አጊሌራ፣ ጆናታን ዊሊያምስ፣ ዳንኤል ሌቪን፣ ሎረን ፕላት፣ አሚ ኦ፣ ማሪሳ ሊዩ፣ ጄሲካ ጉው፣ አሞስ ባታልደን፣ ሊአም ሜይ፣ ቻርሊ ራይሸር፣ አሊሳ ኢሺ፣ ሂሮሺ ኢሺ
ስለ Tangible Media Group የበለጠ ለማወቅ tangible.media.edu ይመልከቱ
Tangible Media Group MIT Media Laboratory፣ 1995 ለማቅረብ
Tangible Media Group ዲጂታል መረጃ እኛ በምንኖርበት የገሀዱ ዓለም ውስጥ የሚካተትብትን እና የሚታቀፍበትን አንድ ዓለም ያስባል፣ ይፈጥራል። የቡድኑ የመጀመሪያ ራዕይ " Tangible Bits" ተጠቃሚዎች ዲጂታል መረጃዎችን ለማግኘት ተራ የሆኑ ግዘፍነት ያላቸውን እቃዎች የመጠቀም ችሎታ እንዲኖራቸው ለማስቻል ያቀደ ነበር። SandScape ከማውዝ እና ከኪቦርድ ይልቅ ዶቃዎችና ብሎኮች ያሉት የአንድ አዲስ Tangible User Interface ምሳሌ ነው።
ለበርካታ ዓመታት የተማሪ ሥራ ሲመለከት የቆየው ኢሺ የ“ Radical Atoms”ን ታላቅ ራዕይ አጎለበተ። inFORM ይህ አዲስ ራእይ እንዲፈጠር ያደረጉት የአንድ ቡድን የምርምር ፕሮጀክቶች ቡድን አንድ አካል ነው። TRANSFORM ይህን አዲስ የምርምር ምዕራፍ ያስጀመረውን ፈር ቀዳጅ ስራ ይገልጻል ወይም ይወክላል። የዚህም ግቡ በስክሪን ላይ ቅርጽን መቀየር እና ልክ እንደ ፒክስሎች ራሳቸውን ኮንፊገር ማድረግ የሚችሉ ቁሶችን ወይም መሳርያዎችን መፍጠር ነበር።
ለዚህ ሥራ አንዱ ወሳኝ ክፍል ኢሺ ለስነጥበብ ያለው ፍቅር ነው። በሱ የራዲካል አተምስ ዲዛይን ፍልስፍና ውስጥ ተማሪዎች "ጠቢብ እና ተንታኝ፣ ሀሳባዊ እና ገቢራዊ" ለመሆን የሚማሩ መሆናቸው መሰረታዊ ነው።
SandScape
Tangible Bits
ያኦ ዋንግ፣ አሳፍ ቢደርማን፣ ቤን ፒፐር፣ ካርሎ ራቲ፣ ሂሮሺ ኢሺ
2003 (የመጀመርያ ዘግጅት)
2022 (ለእይታ የቀረበ ዝግጅት)
SandScape መልክዓ ምድራዊ አቀማመጦችን መጠቀም እንዲችሉ እና ወደ ገጸምድሩ የተንጸባረቁትን የነዚህን ጠቀሜታዎች ውጤቶች እንዲያዩ ያስችልዎታል። መረጃዎችን በቀላሉ ወደ ኮምፒውተር ከማስገባት የዘለለ ተጨባጭ የተጠቃሚ ኢንተርፌስ ነው። የዶቃዎቹን ቅርጾች እና ከፍታዎች ሲቀይሩ የሚታየው የእጆችዎ አካላዊ አንቅስቃሴ ስሌታዊ አምሳያዎችን የሚሰጥ ግብአት ነው። SandScape ውጤቶቹን በተገቢው ጊዜ መረዳት እንድንችል ያግዘን ዘንድ በስሌታዊ ትንታኔ ሃይል አካላዊ ቅርጾችን እንድንጠቀም ተፈጥሯዊ ፍላጎታችንን እና ችሎታችንን ያቀናጃል። መጀመሪያ በ2003 ውስጥ በMIT ሚዲያ ላብ እና በMIT የከተማ ጥናት እና ዕቅድ ክፍል ውስጥ በሚገኘው Senseable City Lab የጋራ ፕሮጀክት ሆኖ የተሠራው SandScape በአዋቂዎችም ሆነ በልጆች ዘንድ ተወዳጅ ኤግዚቢሽን ሆኗል፡
inFORM
ራዲካል አተምስ
ዳንኤል ሊቲንግር፣ ሺን ፎልመር፣ ሂሮሺ ኢሺ
2013 (የመጀመሪያ ዝግጅት)
2025 (ለዕይታ የቀረበ ዝግጅት)
inFORM ከዲጂታል መረጃ ጋር ተጨባጭ በሆነ መንገድ ግንኙነት ማድረግ ማለት ምን ማለት ነው የሚለውን አስቀድሞ የተቀመጡ ድንበሮችን ያሰፋል። ይህ ባይሆን ኖሮ በስክሪን ላይ ብቻ ሊኖሩ ይችሉ የነበሩትን ይዘትና እንቅስቃሴን የሚፈልግ ሲሆን ወደ ገሃዱ ዓለም በማምጣት እና በተገቢው ጊዜ ከመረጃው ጋር መስታግብር እንድንፈጥር በማስቻል በተጨባጭ በ3D እንዲቀርብ ያደርገዋል። ይህ "እየጎለበተ እና እየተቀየር የሚሄድ የቅርጽ ማሳያ" ለከተማ ፕላን ባለሙያዎች 3D ዲዛይኖችን በተጨባጭ ማጋራት የሚችሉበትን መንገድ፣ ለሕክምና ቡድኖች በቀዶ ጥገና ህክምና አምሳያዎች አካላዊ ሙከራ የማድረግ ችሎታ ወይም በአካል ቦታው እንደተገኙ እንዲሰማቸው በቪድዮ ኮንፈረንስ ባለሙያዎቹ በርቀት ተሳትፎ ማድረግ እንዲችሉም ይፈቅድላቸዋል።
inFORM "telepresence"ን፣ የአንድን ተጠቃሚ በርቀት የሚገኙ ግዘፍነት ያላቸውን እቃዎች የመተቀም ችሎታ በተግባር ያሳያል።
ፎቶዎች፡ © 2013 Tangible Media Group/MIT Media Lab
በ2024 የበጋ ወራት በቤተ መዘክሩ ጎብኚዎች ፊት ለፊት inFORM ን ሙሉ በሙሉ አፍርሶ መልሶ የገነባው ቡድን አንድ አካል በመሆኑን ለTangible Media Group ሲሰሩ የነበሩ አራት የMIT የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች። አዲስ የታደሰው ማሽን እንደገና ህዝባዊ ሰርቶ ማሳያዎችን ማድረግ የሚችል ነው።
TRANSFORM
ራዲካል አተምስ (Radical Atoms)
ሂሮሺ ኢሺ፣ ዳንኤል ሊቲንግር፣ ሺን ፎልመር፣ አሚት ዞራን፣ ፊሊፕ ሽውስለር
2014 (የመጀመሪያ ዝግጅት)
2025 (ለእይታ የቀረበ ዝግጅት)
TRANSFORM ግልጽ በሆነ አገላለጽ አንድን የማይንቀሳቀስ የቤት እቃ ወይም ፈርኒቸር ተጠቃሚው ከነገርየው ጋር ባሉት መስተጋብሮች ወደሚመራ እና ለተጠቃሚ መስተጋብሮች ምላሽ ሰጪ ወደ ሆነ አንድ ልዩ ማሽን ይቀይረዋል፣ ያሸጋግረዋል። ከአንድ ሺህ በላይ የሆኑ ፒኖችን እንቅስቃሴ በጥቅሉ በሚቆጣጠሩ ሶስት “ልዩ ቅርጽ ማሳያዎች” የተሰራ ነው። የTRANSFORM ሴንሰር የተጠቃሚውን እንቅስቃሴ በመለየት ፒኖችን በልዩ የሞገድ እንቅስቃሴ ወደ ላይና ወደ ታች እንዲንቀሳቀሱ ያደርጋል። ይህ ስራ ተፈጥሮ ውስጥ ነፋስ፣ ውሃና አሸዋ በጋራ በሚያደርጉት መስተጋብር እንዲሁም በተፈጥሮ እና በማሽን መካከል ሊኖር በሚችለው ትብብር መነሻነት የተሰራ ነው።