

የተግባራት ቅደም ተከተል (Sequence of Actions)
በ 1920 ዎቹ አጋማሽ እና በ 1970 ዎቹ አጋማሽ መሃከል ላይ በ MIT የበለጸጉት እና ስራ ላይ የዋሉት Differential Analyzer፣ Whirlwind ኮምፒውተር እና Apollo Guidance በኮምፒውቲንግ ታሪክ ውስጥ ጎልተው የሚታዩ ስራዎች ናቸው። እነዚህ ትልልቅ እና ውስብስብ ፕሮጀክቶች ሆነው በደርዘን የሚቆጠሩ፣ ኋላም በመቶዎች ከዛም በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎቹን ያሳተፉ ነበሩ። አንድ ላይ እነዚህ ግለሰቦች አሁን ላይ ባለው የዲጂታል ዓለም ዕድገት ላይ እጅግ ወሳኝ ሚና የሚጫወት የተለየ ማሕበረሰብ የፈጠሩ ናቸው። የ MIT ሙዝየም የነዚህን ታሪካዊ የኮምፒዩቲንግ ማሽኖች የሚሰሩ አምሳያዎች፣ ኢሙሌተሮች እና ሲሙሌተሮች ለመፍጠር ያለመ እያደገ ያለ እንቅስቃሴ አካል ሆኗል። ጥረቶቹም ውጤት እያሳዩ ይገኛሉ። በዚህ የመጀመሪያ፣ “ተከታታይነት ያላቸው ተግባራት” ን ዲኮድ ለማድረግ እና ለመተርጎም የተደረገ ሙከራ-ግዑዝ የሆኑ ማሽኖች- በአንዴ አንድ ትንሽ ችግር- ህልመኛ የሆኑ አንድን ሀገር ለማነቃቃት፣ ብሄራዊ የመከላከያ መረብ ለመፍጠር እና የሰው ልጆችን ጨረቃ ላይ የማሳረፍ ጥረቶች ላይ ቁልፍ ሚና መጫወትን የሚሹ መሃንዲሶች መርዳቱ፣ ሁሉም እናውቀዋለን ብለን ይዘነው የነበረ ነገር ላይ ተጽዕኖ ያሳደረ ነበር።