Skip to content

MIT ይሰበስባል (MIT Collects)

MIT ያስተምራል። MIT ምርምር ያካሂዳል። MIT ይፈጥራል። እና MIT ይሰበስባል። MIT አንድ ያልተለመደ ፕሮጀክት 1971 ላይ አካሄደ፤ የተቋሙን ስራ እና ህይወት የሚሰንድ የእጅ ስራዎች ስብስብ አዘጋጀ። ዛሬ፣ የ MIT ሙዝየም ስብስብ፣ ከ sublime እስከ silly ከ 1.5 ሚልዮን በላይ የሆኑ ዕቃዎች አሉት። ስለ ዘመናዊው ዓለም ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ስነ-ጥበብ እና ትምህርት እጅግ በጣም አስደናቂ እና ፈታኝ የሆኑ ታሪኮችን ይተርካሉ። የሙዚየሙ ተልዕኮ ጠበቆ ከማቆየት በላይ ነው። ስብስቡ በተመለከተ ያለን ግብ ሁሌም ቢሆን አሁን ላይ በ MIT ማሕበረሰብ እየተካሄዱ ላሉ ጥረቶች አጋዥ እንዲሆን ነው፦ አዲስ እውቀትን ለመፍጠር እና ለማሰራጨት እና የተሻለ ዓለምን ለመፍጠር የሚደረጉ ጥረቶችን እንዲያግዙ እንሻለን። አሁን የ MIT ስብስብን ከእናንተ ጋር ማጋራት እንሻለን። ይህ የስነ-ጥበብ ስራዎች ስብስብ የሃብት የተካበተበት ቤት እኛ መሳሪያም ነው። መደበኛ በሆነ መልኩ ኤግዚብሽኖችን፣ ዎርክሾፖችን እና መርሃ-ግብሮችን በመቀየር፣ የ MIT ስብስብ ይበልጥ ተደራሽ እንዲሆን የማድረግ ህልም አለን። ማሳያዎቹ ወደ የእጅ ስራዎቹ እና ሀሳቦች መግቢያ እና የእርስዎን አይነህሊና ለማነቃቃት የተቀመጡ ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ ስለ ስብስቦቹ ታሪክ ይናገራሉ፦ እንዴት ዕቃዎቹን እንዳገኘናቸው፣ እንደምንንከባከባቸው፣ እና ለእይታ እንድምናቀርባቸው የሚያስረዱ ናቸው። የፈጠራ ችሎታዎን እንደምናበረታታም ተስፋ እናደርጋለን። ስብስቦቹን ለትምህርት፣ ምርምር፣ ንግድ፣ መዝናኛ፣ ስነ-ውበታዊ አድናቆት፣ ወይም ለፈለጉት ዓላማ ይጠቀሙባችው ዘንድ፣ ስብስቦቹን በቀላሉ እንዲያገኙ እና ጥቅም ላይ እንዲያውሉ ማድረግ። ይህ ስብስብ ዕቃ ላይ ማዕከል ያደረገ፣ ዕውቀትን የሚሻ የእጅ ስራ ስብስብ እና ህልቆ መሳፍርት አዳዲስ ሃሳቦች እና እይታዎች የሚፈጠሩበት ስፍራ እንዲሆን ያግዙን። የተለየ ማስታወሻ ካልተቀመጠላቸው በቀር፣ ሁሉም በማሳያው ላይ የሚገኙ የእጅ ስራዎች እና ስእሎች ከ MIT ስብስቦች የመጡ ናቸው።